ደንበቦች እና ሁኔታዎች
የአጠቃቀም ደንቦች ላይ የሚኖሩ ለውጦች
እነዚህን የአጠቃቀም ደንቦች በእኛ ምርጫ ከጊዜ ወደ ጊዜ ልንከልስ እና ልናዘምን እንችላለን። ሁሉም ለውጦች በምናሳውቅበት ጊዜ ወዲያውኑ ስራ ላይ ይውላሉ፤ የድረ-ገፁ አገልግሎት እና አጠቃቀም ላይም ይተገበራሉ።
የተሻሻለውን የአጠቃቀም ደንብ መውጣት ተከትሎ ድረገጹን መጠቀም ከቀጠሉ ለውጦቹን ተቀብለዋል ማለት ነው። ማንኛቸውም ለውጦች በእርስዎ ላይ ተተግባሪ እንደሚሆኑ ለማወቅ ይህን ገጽ ከጊዜ ወደ ጊዜ መመልከት ይጠበቅብዎታል።
ድረ ገጹን ስለመጠቀም እና የአካውንት ደኅንነትን በተመለከተ
ድረ ገጹን እና በድረ ገጹ ላይ የምናቀርበውን ማንኛውንም አገልግሎት ወይም ይዘት በኛ ብቸኛ ውሳኔ ያለማሳወቂያ የማቋረጥ ወይም የማሻሻል መብታችን የተጠበቀ ነው። በማንኛውም ምክንያት ሁሉም ወይም የትኛውም የድረ-ገጹ ክፍል በማንኛውም ጊዜ የማይገኝ ከሆነ ተጠያቂ አንሆንም። ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ የድረ-ገጹን አንዳንድ ክፍሎች፣ ወይም መላውን ድረ ገጽ፣ ለማንኛውም ተጠቃሚ ተደራሽ እንዳይሆን ልንገድበው እንችላለን።
የእርስዎ ሃላፊነት የሆኑት፡-
- ድረ ገጹን እንዲጠቀሙ ሁሉንም አስፈላጊ ዝግጅቶች ማድረግ።
- በበይነ መረብ ግንኙነትዎ ድረ ገጹን የሚያገኙ ሁሉም ሰዎች እነዚህን የአጠቃቀም ደንቦች እንደሚያውቁ እና እነሱን እንደሚያከብሩ ማረጋገጥ።
ድረ ገጹን ወይም አንዳንድ የሚያቀርባቸውን ግባቶችን ለማግኘት ወደ ድረ-ገጹ የሚያስገቧቸው መረጃዎች በሙሉ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መሆናቸው ድረ-ገጹን ለመጠቀም ቅድመ ሁኔታ ነው። በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ማንኛውንም ኢንተራክቲቭ ስሪቶችን በመጠቀም ወይም ፍላጎትዎን በመመዝገብ ላይ ጨምሮ በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚያቀርቡት ሁሉም መረጃዎች በእኛ የግላዊነት ፖሊሲ የሚተዳደሩ መሆናቸውን እና መረጃዎን በተመለከተ ለምናደርጋቸው እርምጃዎች ሁሉ በግላዊነት ፖሊሲያችን አማካኝነት መሆናቸውን ይስማማሉ።
የአዕምሮ ንብረት መብት
ድህረ ገጹ እና አጠቃላይ ይዘቱ፣ ስሪቶቹ እና አሰራሩ (ሁሉንም መረጃ፣ ሶፍትዌር፣ ጽሑፍ፣ ማሳያዎች፣ ምስሎች፣ ቪዲዮ እና ኦዲዮ እና ዲዛይን፣ ምርጫ እና አደረጃጀት ጨምሮ) በኩባንያው፣ በላይሰንስ ሰጪዎቹ ወይም ሌሎች የዚህ አይነት ይዘት አቅራቢዎች የተያዙ ሲሆኑ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና በአለም አቀፍ የቅጂ መብት፣ የንግድ ምልክት፣ የፈጠራ ባለቤትነት፣ የንግድ ሚስጥር እና ሌሎች የአእምሯዊ ንብረት ወይም የባለቤትነት መብቶች ህጎች የተጠበቁ ናቸው።
እነዚህ የአጠቃቀም ደንቦች ድረገጹን ለግል ወይም ለንግድ ላልሆነ አገልግሎት ብቻ እንዲጠቀሙ ይፈቅድሎታል። በድረ-ገጻችን ላይ ከሚከተሉት በስተቀር ማባዛት፣ ማሰራጨት፣ ማሻሻል፣ ከድረገጹ ጽንሰሃሳብ የሚነሱ ስራዎችን መፍጠር፣ በይፋ ማሳየት፣ በይፋ ማከናወን፣ እንደገና ማተም፣ ማውረድ፣ ማከማቸት ወይም ማስተላለፍ የለብዎትም።
- ኮምፒውተሮ የተጠቀሱትን ከማግኘቶ እና ከማየትዎ አንጻር የእንደዚህ አይነት ይዘቶችን በጊዜያዊነት በ RAM ውስጥ ሊያከማች ይችላል።
- ለእይታ ማሻሻያ ዓላማ በድር አሳሽዎ በአዎቶማቲክ የተያዙ ፋይሎችን ሊያከማቹ ይችላሉ።
- ለግል ወይም ለንግድ ላልሆነ አገልግሎት ውስን ለሆነ ምክንያታዊ ግዜ ሊያባዙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ለመልሶ ማዘጋጀት ፣ ለማሳተም ወይም ለማሰራጨት መሆን አይችልም።
- አውርደው ይጠቀሙባቸው ዘንድ የዴስክቶፕ፣ ሞባይል ወይም ሌሎች መተግበሪያዎችን ካቀረብን አንድ ቅጂ ወደ ኮምፒውተርዎ ወይም ሞባይሎ ለግልዎ ወይም ለንግድ ላልሆነ አገልግሎት ብቻ በማውረድ ለእንደዚህ አይነት መተግበሪያዎች በእኛ የተጠቃሚ ላይሰንስ ስምምነቶች ለመገዛት ተስማምተዋል።
- ማህበራዊ ሚዲያ ስሪቶችን ከተወሰኑ ይዘቶች ጋር ካቀረብን እንደስሪቶቹ አገልግሎት ሊጠቀሙ ይችላሉ።
ማድረግ የሌለብዎት
- ከዚህ ድረ ገጽ ማንኛውንም ይዘት ቅጂዎች ማስተካከል።
- የድረ-ገጹን ማንኛውንም ክፍል በሌላ ድረ ገጽ ላይ፣ በሌላ በማንኛውም ሚዲያ (በህትመት፣ በኤሌክትሮኒክስ ወይም በሌላ) ወይም እንደ ማንኛውም የንግድ አገልግሎት አካል እንደገና ማተም።
- ማንኛውንም ሥዕላዊ መግለጫዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ቪዲዮ ወይም ኦዲዮ ፋይሎችን ወይም ማንኛውንም ግራፊክስ አብሮት ከተያያዘው ጽሑፍ ነጥሎ መጠቀም።
- ከዚህ ድረገጽ ይዘት የተገኙ ማንኛውም የቅጂ መብት፣ የንግድ ምልክት ወይም ሌላ የባለቤትነት መብት ማስታዎቂያ ቅጂዎችን መሰረዝ ወይም መቀየር።
በድረ ገጹ ላይ ያለ ማንኛውም ይዘት ፣ መብት ፣ ርዕስ ወይም ፍላጎት ወደ እርስዎ አይተላለፍም፤ እና ሁሉም በግልጽ ያልተሰጡ መብቶች በኩባንያው የተጠበቁ ናቸው። በነዚህ የአጠቃቀም ውሎች በግልጽ ያልተፈቀደ ማንኛውም የድረ-ገጹ አጠቃቀም የእነዚህን የአጠቃቀም ደንቦች መጣስ እና የቅጂ መብት፣ የንግድ ምልክት እና ሌሎች ህጎችን ሊተላለፍ ይችላል።
የንግድ ምልክቶች
የኩባንያው ስሞች ፣ የምርት ስሞች ፣ የኩባንያው አርማዎች እና ሁሉም ተዛማጅ ስሞች ፣ አርማዎች ፣ የምርት እና የአገልግሎት ስሞች ፣ ንድፎች እና መፈክሮች የኩባንያው ወይም ተባባሪዎቹ ወይም የፍቃድ ሰጪዎቹ የንግድ ምልክቶች ናቸው ። ከኩባንያው የጽሁፍ ፈቃድ ውጭ ምልክቶችን መጠቀም አይችሉም። በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ያሉ ሁሉም ሌሎች ስሞች፣ አርማዎች፣ የምርት እና የአገልግሎት ስሞች፣ ንድፎች እና መፈክሮች የየባለቤቶቻቸው የንግድ ምልክቶች ናቸው።
በቀጥታ እርስዎ ለእኛ ሲሰጡን
- በድረገጹ ውስጥ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አውቶማቲካዊ በሆነ መልኩ የሚሰበሰበው መረጃ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡- የአጠቃቀም ዝርዝሮችን፣ የአይፒ አድራሻዎችን እና በኩኪዎች አማካኝነት የተሰበሰበ መረጃ፣ ዌብ ቢኮኖች እና በሌሎች የመከታተያ ቴክኖሎጂዎች የተሰበሰበ መረጃን።
- ከሶስተኛ ወገኖች ለምሳሌ የንግድ አጋሮቻችን።
የተከለከሉ አጠቃቀሞች
ድረ ገጹን ለሕጋዊ ዓላማዎች ብቻ እና በእነዚህ የአጠቃቀም ደምብ መሠረት መጠቀም ይችላሉ። ድረ ገጹን በሚከተሉት መልኩ ላለመጠቀም ይስማማሉ፡-
- በማንኛውም መልኩ ማንኛውንም የሚመለከተውን የፌደራል፣ የአካባቢ ወይም አለም አቀፍ ህግ ወይም ደንብ የሚጥስ፣ ገደብ አልባነትን ጨምሮ።
- ማንኛውንም “የማይረባ መልእክት”፣ “ወደሰው ሚሰራጭ ደብዳቤ” ወይም “አይፈለጌ መልእክት” ወይም ሌላ ማንኛውንም ተመሳሳይ መጠይቆችን ጨምሮ ማንኛውንም የማስታወቂያ ወይም የማስተዋወቂያ ይዘትን ለማስተላለፍ ወይም ለማዘጋጀት።
- ኩባንያውን፣ የኩባንያውን ሰራተኛ፣ ሌላ ተጠቃሚ ወይም ሌላ ሰው ወይም አካልን ለማስመሰል ወይም ለማስመሰል ለመሞከር (ያለምንም ገደብ ከላይ ከተጠቀሱት ማናቸውም ጋር የተያያዙ የኢሜይል አድራሻዎችን ወይም የስክሪን ስሞችን መጠቀምን ጨምሮ)።
- የማንንም ሰው የድረ-ገጹን አጠቃቀም ወይም በድረገጹ መደሰትን የሚገድብ ወይም የሚከለክል ወይም በእኛ እንደተወሰነው ኩባንያውን ወይም የድረ-ገጹን ተጠቃሚዎችን ሊጎዳ ወይም ለተጠያቂነት ሊያጋልጥ በሚችል በማንኛውም ሌላ ምግባር ውስጥ ለመሳተፍ።
በተጨማሪም፣ የሚከተሉትን ላለማድረግ ይስማማሉ፡-
- በማንኛውም መንገድ ገጸ ድሩን ሊያሰናክል፣ ሊያጨናንቅ፣ ሊጎዳ ወይም ሊያበላሽ የሚችል ወይም የሌላ አካልን የድረ-ገፁን አጠቃቀም ሊያደናቅፍ በሚያስችል መልኩ እና በድረ-ገጹ በኩል በአሁናዊ ሁኔታ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍ ችሎታቸውን ማስተጓጎል።
- ድረ ገጹን ለማንኛውም ዓላማ ለመጠቀም ማንኛውንም ሮቦት፣ ስፓይደር ወይም ሌላ አውቶማቲክ መሳሪያ መጠቀም፣ በድረ-ገጹ ላይ ያለውን ማንኛውንም ይዘት መከታተል ወይም መቅዳትን ጨምሮ።
- እኛ በምንሰጠው በጽሁፍ ባልተደገፈ ፍቃድ በድረ-ገጹ ላይ ወይም ለሌላ ላልተፈቀደ ዓላማ ማንኛውንም ይዘት ለመከታተል ወይም ለመቅዳት ማንኛውንም ማኑዋል ሂደት መጠቀም።
- የድረ-ገጹን ትክክለኛ አሠራር የሚያደናቅፍ ማንኛውንም መሳሪያ፣ ሶፍትዌር ወይም ተግባር መጠቀም።
- ማናቸውንም ቫይረሶች፣ ትሮጃን ሆርሥ፣ ወርሞች፣ ሎጂክ ቦምቦች ወይም ሌሎች ተንኮል-አዘል ወይም የቴክኖሎጂ ጎጂ የሆኑ ነገሮችን ማስገባት።
- ባልተፈቀደ ሁኔታ የድረ-ገጹን ክፍሎች፣ ድህረ ገጹ የተከማቸበትን ሰርቨር ፣ ወይም ከድህረ ገጹ ጋር የተገናኘ ማንኛውንም ሰርቨር፣ ኮምፒውተር ወይም ዳታቤዝ ለማግኘት፣ ጣልቃ ለመግባት፣ ለመረበሽ ወይም ለማበላሸት መሞከር።
- ድረ ገጹ ላይ የአገልግሎት መግቻ ወይም የተሰራጨ የአገልግሎት መግቻ ጥቃት ማድረስ
- ወይም የድረ-ገጹን ትክክለኛ አሠራር ለማደናቀፍ መሞከር።
በተለጠፈው መረጃ ላይ መተማመን መቻል
በድረ-ገጹ ላይ ወይም በድረ-ገጹ በኩል የቀረበው መረጃ ለአጠቃላይ መረጃ አገልግሎት ብቻ ነው። የዚህን መረጃ ትክክለኛነት፣ ሙሉነት ወይም ጠቃሚነት ዋስትና አንሰጥም። የዚህን መረጃ ትክክለኛነት፣ ሙሉነት ወይም ጥቅም ዋስትና አንሰጥም። በሚቀርቡት መረጃዎች የሚተማመኑት በራስዎ ሃላፊነት ብቻ ይሆናል ። በእርስዎ ወይም በሌላ የድረ-ገጹ ጎብኚ ወይም ስለ ይዘቱ የሚነገረው ማንኛውም ሰው በእንደዚህ አይነት ይዘቶች ላይ ከተጣለ ማንኛውም አይነት ጥገኝነት የተነሳ ሁሉንም ተጠያቂነት እና ሃላፊነት ውድቅ እናደርጋለን።
ድረ ገጹን ማዘመን
በድረ-ገጹ ላይ ያለውን ይዘት ከጊዜ ወደ ጊዜ ልናዘምነው እንችላለን፣ ነገር ግን ይዘቱ የግድ የተሟላ ወይም ወቅታዊ አይደለም። በድረ-ገጹ ላይ ያለው ማንኛውም ይዘት በማንኛውም ሰዓት ላይ ጊዜው ያለፈበት ሊሆን ይችላል እናም ይዘቶቹን የማዘመን ግዴታ የለንም።
ስለእርስዎ እና ወደ ድህረ ገጹ ስላደረጓቸው ጉብኝቶች መረጃ
በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የምንሰበስበው ሁሉም መረጃ ለግላዊነት መመሪያችን ተገዢ ነው። ድረ ገጹን በሚጠቀሙበት ወቅት መረጃዎን በተመለከተ የግላዊነት መመሪያውን ባማከለ መልኩ በእኛ በሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ ይስማማሉ።
ከድረ ገጹ እና ከማህበራዊ ሚዲያ ስሪቶች ጋር ማገናኘት
ፍትሃዊ እና ህጋዊ በሆነ መንገድ ስማችንን በማይጎዳ ወይም ራስ ወዳድ ባልሆነ መንገድ እስካልተጠቀሙ ድረስ ማንኛውንም ገፅ በማስፈንጠሪያ ማገናኘት ይችላሉ ፤ ነገር ግን የትኛውንም አይነት ዝምድናን ለመጠቆም ፣ ከኛ ፍቃድን ወይም ድጋፍን እንዳገኙ በማስመሰል ማገናኘት አይችሉም።
ይህ ድህረ ገጽ የሚከተሉትን እንዲያደርጉ የሚያስችሉዎትን አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ስሪቶችን ሊያቀርብ ይችላል።
- ከራስዎ ወይም ከተወሰኑ የሶስተኛ ወገን ድረ-ገጾች ወደ አንዳንድ ይዘቶች በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ማገናኘት።
- በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ኢሜይሎችን ወይም ሌሎች ግንኙነቶችን ከተወሰነ ይዘት ጋር ወይም ወደ አንዳንድ ይዘቶች የሚወስዱ አስፈንጣሪዎችን መላክ መቻል።
- በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የተገደቡ የይዘት ክፍሎች በራስዎ ወይም በተወሰኑ የሶስተኛ ወገን ድረ ገጾች ላይ እንዲታዩ ወይም መስለው እንዲታይ ማድረግ።
እነዚህን ስሪቶች በእኛ እንደተሰጡበት ሁኔታ ብቻ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉት አብሯቸው ከሚታየው ይዘት አንጻር እና በሌላ መልኩ በነዚህ ባህሪያት በምናቀርባቸው ተጨማሪ ደንቦች እና ሁኔታዎች መሰረት ነው። ከላይ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፡-
- የእርስዎ ካልሆነ ከማንኛውም ድር ድረ ገጽ ማስፈንጠሪያ ማዘጋጀት።
- በዚህ ድረ ገጽ ላይ ካሉት ሌሎች የአጠቃቀም ደንቦች ጋር የማይጣጣም ማንኛውንም እርምጃ አይውሰዱ።
ማንኛውም ያልተፈቀደ አገላለጽ ወይም ግንኙነት ወዲያውኑ እንዲቆም ለማድረግ ከእኛ ጋር ለመተባበር ተስማምተዋል። የማስፈንጠሪያ ፈቃዱን ያለማሳወቂያ የማቋረጥ መብታችን የተጠበቀ ነው።
ሁሉንም ወይም ማንኛውንም የማህበራዊ ሚዲያ ስሪቶችን እና ማናቸውንም ማስፈንጠሪያዎች በማንኛውም ጊዜ ያለማሳወቂያ በኛ ውሳኔ ማቋረጥ እንችላለን።
ከድረ ገጹ የሚመጡ ማስፈንጠሪያዎች
ድረ-ገጹ ወደ ሌሎች ገፆች እና በሶስተኛ ወገኖች የተሰጡ ግብዓቶችን ከያዘ፣ እነዚህ ማስፈንጠሪያዎች ለእርስዎ ምቾት ብቻ የቀረቡ ናቸው። ይህ ባነር ማስታወቂያዎችን እና ስፖንሰር የተደረጉ ማስፈንጠሪያዎችን ጨምሮ በማስታወቂያዎች ውስጥ የተካተቱ ማስፈንጠሪያዎችን ያካትታል። በእነዚያ ድረ ገጾች፣ ግብዓቶች ወይም ይዘቶች ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር የለንም፣ እና ለእነሱም ሆነ እርስዎ በመጠቀሞ ለሚደርስብዎ ክስረት ወይም ጉዳት ምንም አይነት ኋላፊነት አንወስድም። ከዚህ ድህረ ገጽ ጋር የተገናኙትን የሶስተኛ ወገን ድረ-ገጾችን ለማሰስ ከወሰኑ፣ ሙሉ በሙሉ በራስዎ ሃላፊነት ሲሆን ለእንደዚህ አይነት ድረ-ገጾች የአጠቃቀም ደንቦችን ተገዢ በመሆን ነው።
የጂኦግራፊያዊ ገደቦች
የድህረ ገጹ ባለቤት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ ነው የሚገኘው። ድህረ ገጹ ወይም ይዘቱ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ውጭ ተደራሽ ወይም ተገቢ ነው ብለን አናረጋግጥም። የድረ-ገጹን መጎብኘት በተወሰኑ ሰዎች ወይም በተወሰኑ ሀገሮች ህጋዊ ላይሆን ይችላል። ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውጭ ሆነው ድህረ ገጹን ከጎበኙ፣ በራስዎ ተነሳሽነት ያደረጉት ነገር ሲሆን የአካባቢዎን ህጎችን የማክበር ሀላፊነት አለብዎት።
የዋስትናዎች ማስተባበያ
ድረ ገጹ ከቫይረሶች ወይም ከሌላ አጥፊ ኮድ ነፃ እንደሚሆን ዋስትና መስጠት እንደማንችል እና ዋስትና እንደማንሰጥ ይረዱ። ለፀረ-ቫይረስ ጥበቃ እና የውሂብ መግባት እና መውጣት ትክክለኛነት የእርስዎን ልዩ መስፈርቶች ለማሟላት እና የጠፋውን ማንኛውንም መረጃ መልሶ ለመገንባት ከድረ-ገጻችን ውጭ ያለውን ዘዴ ለመጠበቅ በቂ ሂደቶችን እና የፍተሻ ነጥቦችን የመተግበር ሃላፊነት አለብዎት።
በተከፋፈለ የሰርቪስ ዲናያል ጥቃት በተከሰቱ ፣ ቫይረሶች ወይም በሌሎች ቴክኖሎጂያዊ ጎጂ ይዘቶች አማካኝነት የኮምፒዩተርዎን መሳሪያ ፣ እና ፐሮግራም ሲቆጣጠሩ ድረ-ገጹን ሲጠቀሙ ወይም በድረ-ገጹ ላይ የተለጠፈ ማንኛውንም ይዘት ሲያወርዱ ወይም ከእሱ ጋር በተገናኘ ማንኛውም ድህረ ገጹ ላይ የተገኙ አገልግሎቶችን ወይም እቃዎች ሲጠቀሙ ለሚደርሰው ኪሳራ ወይም ጉዳት ተጠያቂ አንሆንም።
ድረ-ገጹን ፣ ይዘቱን እና በድረ-ገጹ በኩል የተገኙ አገልግሎቶች ወይም ቁሶችን የሚጠቀሙት በራሶ ሃላፊነት ነው። ድረ ገጹ፣ ይዘቱ እና በድረ-ገጹ በኩል የተገኙ ማናቸውም አገልግሎቶች ወይም እቃዎች በ”እንዳሉበት ሁኔታ” እና “በሚገኙበት ግዜ” መሰረት ያለ ምንም አይነት በሚገለጽም ሆነ በሚደረግ ዋስትናዎች ይሰጣሉ። ኩባንያውም ሆነ ከኩባንያው ጋር የተጎዳኘ ሰው ድረ-ገጹ ሙሉነት፣ ደህንነት፣ አስተማማኝነት፣ ጥራት፣ ትክክለኛነት ወይም ተገኝነት ምንም አይነት ዋስትና ወይም ውክልና አይሰጥም። ከላይ የተገለጸውን ሳይገድብ፣ ኩባንያውም ሆነ ከኩባንያው ጋር የተገናኘ ማንም ሰው ከድረ ገጹ የተገኙ፣ ይዘቶች ወይም ማንኛቸውም አገልግሎቶች ወይም እቃዎች ትክክለኛ፣ አስተማማኝ፣ ከስህተት የጸዳ ወይም ያልተቋረጠ፣ ጉድለቶች የሚስተካከሉበት ይሆናሉ ብለው አይወክሉም ወይም ዋስትና አይሰጡም። በተጨማሪም ድረ ገጹ ወይም እንዲገኝ የሚያደርገው ሰርቨር ከቫይረሶች ወይም ሌሎች ጎጂ ክፍሎች የጸዳ ነው ወይም ድረ ገጹ ማንኛውንም የአገልግሎት ፍላጎቶችዎን ወይም የሚጠበቁትን ያሟላል ተብሎ ዋስትና አይሰጥም።
በማንኛዉም የጥሰት ዋስትናዎችን ሳይገደብ በማካተት ኩባንያው በዚህ መልኩ ማንኛውንም አይነት ዋስትናዎች ፣ ግልፅም ሆነ ድርጊታዊ ፣ህጋዊም ሆነ ሌላ ማንኛውንም ዋስትናዎች ውድቅ ያደርጋል።
ቀደም ሲል የተገለጸው ነገር በሚመለከተው ህግ ሊገለሉ ወይም ሊገደቡ የማይችሉ ማንኛውንም ዋስትናዎችን አይነካም።
በተጠያቂነት ላይ ገደብ
በምንም አይነት ሁኔታ ኩባንያው፣ ተባባሪዎቹ ወይም ፍቃድ ሰጪዎቻቸው፣ አገልግሎት ሰጪዎቻቸው፣ ሰራተኞች፣ ወኪሎች፣ መኮንኖች ወይም ዳይሬክተሮች በህጋዊ ፅንሰ-ሀሳብ ስር በእናንተ ውስጥ በሚፈጠር ለማንኛውም አይነት ጉዳት ፣ ድረገጹን ወይም ከርሱጋር የተገናኘን አጠቃቀም ወይም መጠቀም አለመቻልን አስመልክቶ ተጠያቂ አይሆኑም። በተጨማሪም በድረ-ገጹ ላይ ያለ ማንኛውም ይዘት ወይም በመሰል ሌሎች ድረገጾች ወይም ማንኛውም አገልግሎቶች ወይም እቃዎች በድረ-ገጹ ወይም በመሰል ድረ-ገጾች በኩል የተገኘ ማንኛውም አይነት ቀጥተኛ፣ ቀጥተኛ ያልሆነ፣ ልዩ፣ ድንገተኛ፣ ተላላፊ፣ ቀጪ ጉዳትን ጨምሮ ግን በተጨማሪም በሚከተሉት ሳይወሰን፡- የግል ጉዳት፣ ህመም እና ስቃይ፣ ስሜት መረበሽ፣ የገቢ ማጣት፣ ትርፍ ማጣት፣ የንግድ ኪሳራ ወይም የተጠበቀውን ቁጠባ ማጣት፣ አገልግሎትን ማጣት፣ በጎ ፈቃድ ማጣት፣ የውሂብ መጥፋት እና ማዛባት (ንዝህላልነትን ጨምሮ) ፣ ውልን መጣስ ወይም አለበለዚያ፣ አስቀድሞ የሚታወቅ ቢሆንም ተጠያቂ አይሆኑም።
ከላይ የተጠቀሰው በሚመለከተው ህግ ሊገለል ወይም ሊገደብ የማይችል ማንኛውንም ተጠያቂነት አይነካም
ማካካሻ
ኩባንያውን፣ ተባባሪዎቹ፣ ፍቃድ ሰጪዎቹ እና አገልግሎት ሰጪዎቹ፣ እና የየራሳቸው ኦፊሰሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ሰራተኞች፣ ተቋራጮች፣ ወኪሎች፣ ፍቃድ ሰጪዎች፣ አቅራቢዎች፣ ተተኪዎች እና ሹመኞች ከማንኛውም የይገባኛል ጥያቄዎች፣ እዳዎች፣ ኪሳራዎች፣ ፍርዶች፣ ሽልማቶች፣ ኪሳራዎች፣ ወጪዎች ወይም ክፍያዎች (ተመጣጣኝ የጠበቆች ክፍያዎችን ጨምሮ) እዚህን የአጠቃቀም ደንብ በመጣስዎ ወይም በድረ-ገጹ አጠቃቀምዎ ምክንያት ወይም በተዛመደ እና በነዚህ የአጠቃቀም ደንቦች ወይም በእርስዎ የተፈቀደ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውንም የድረ-ገፁን ይዘት ፣ አገልግሎቶች እና ምርቶች አጠቃቀም በተመለከተ ከድረ ገጹ የተገኘ ማንኛውንም መረጃ ከመጠቀም ለመከላከል ይስማማሉ።
ገዢ ህግ እና ስልጣን
ከድረ-ገጹ ጋር የተያያዙ ሁሉም ጉዳዮች እና እነዚህ የአጠቃቀም ደንቦች እና ማንኛውም ክርክር ወይም የይገባኛል ጥያቄ ከድረገጹ ጋር የተዛመደ (በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ፣ ከውል ውጪ የሆኑ አለመግባባቶችን ወይም የይገባኛል ጥያቄዎችን ጨምሮ)፣ በውስጥ ተፈፃሚነት ባላቸው ህጎች መሰረት በዱባይ ኢሚሬትስ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ማንኛውንም ምርጫ ወይም የህግ ድንጋጌ ወይም ደንብ (የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ወይም ሌላ ማንኛውንም ስፍራ) መተዳደር እና መተርጎም አለበት።
ከዚህ የአጠቃቀም ደምብ ወይም ድረ-ገጹ ላይ የሚነሳ ማንኛውም የህግ ክስ፣ ድርጊት ወይም ሂደት በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፍርድ ቤቶች ብቻ ቢመሰረትም በሚኖሩበት ቦታ ወይም በሚኖሩበት ሀገር ወይም በሌላ በማንኛውም ሀገር ውስጥ እነዚህን የአጠቃቀም ውሎች መጣስ በእርስዎ ላይ ማንኛውንም ክስ ወይም የፍርድ ሂደት የማቅረብ እንደዚህ ባሉ ፍርድ ቤቶች በእርስዎ ላይ ያለውን የስልጣን አጠቃቀም እና በእንደዚህ ያሉ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ያሉትን ማንኛውንም እና ሁሉንም ተቃውሞዎች ይተዋሉ።
የይገባኛል ጥያቄዎችን ለማቅረብ በጊዜ ላይ ያለው ገደብ
ከእነዚህ የአጠቃቀም ውል ወይም ድረ ገፁ ጋር በተያያዙ ማናቸውም የእርምጃዎች ወይም የይገባኛል ጥያቄዎች በአንድ (1) አመት ጊዜ ውስጥ መጀመር አለበት ያለበለዚያ፣ እንደዚህ አይነት ድርጊት ወይም ንግርት ለዘለቄታው ይታገዳል።
የመተው እና የማቋረጥ ችሎታ
በእነዚህ የአጠቃቀም ደምብ ውስጥ የተመለከቱትን ማንኛውንም ውሎች ወይም ቅድመ ሁኔታዎች በኩባንያው የሚሰጥ ማቋረጫ እንደ ተጨማሪ ወይም ቀጣይነት ያለው ቃል ወይም ሁኔታ ወይም ሌላ ማንኛውንም ደምብ ወይም ሁኔታ መሻር ተደርጎ አይቆጠርም። እና በዚህ የአጠቃቀም ደምብ መሰረት የኩባንያው ማንኛውም መብት ወይም ጥቅማጥቅም ለማስረዳት አለመቻል በነዛ መብት ወይም ጥቅማጥቅም ማሳለፍን አይገልጽም።
ከእነዚህ የአጠቃቀም ደንቦች በፍርድ ቤት ወይም በሸንጎ ተቀባይነት የሌለው፣ ህገወጥ የሆነ ወይም በማንኛውም ምክንያት የማይተገበር ከሆነ፣ ይህ ድንጋጌ ይሰረዛል ወይም በዝቅተኛ ገዢ ሃይሉ ተገድቦ የቀረው ክፍሉ በሙሉ ኃይል እና ውጤት እያገለገለ ይቀጥላል።
ሙሉ ስምምነት
የአጠቃቀም ደምብ፣ የግላዊነት ፖሊሲያችን እና የንብረት ስምምነቱ ድረ ገጹን በተመለከተ በእርስዎ እና በኩባንያው መካከል ብቸኛው እና አጠቃላይ ስምምነትን በመመስረት ሁሉንም የቀድሞ እና ወቅታዊ ግንዛቤዎችን ፣ ስምምነቶችን ፣ ውክልናዎችን እና ዋስትናዎችን በጽሑፍ እና በቃል ይተካል። ከድር ጣቢያው አኳያ።
የርስዎ አስተያየት እና ስጋቶች
ይህ ድረ ገጽ በድርጅቱ ባለቤትነት ስር ይተዳደራል።
የቴክኒክ ድጋፍ ጥያቄዎችን እና ከረ ገጹ ጋር የተያያዙ ሌሎች ግንኙነቶችን በተመለከተ፣ የድረ-ገፃችንን አድራሻ በመጠቀም ወይም info@eaglehills.com አድራሻ በኢሜል በመላክ ሊያገኙን ይችላሉ።
ለአስተያየት እና ምክር እባክዎትን በ info@eaglehills.com በኩል ያግኙን
ይህን ድረ ገጽ በመጠቀም የግል መረጃዎን ፣ አድራሻዎን መረጃዎን በማዘመን፣ በመቀየር ወይም በማስተካከል፣ ኩባንያው ወይም ማናቸውም አጋሮቹ በእነሱ ምርጫ እንደዚህ ያሉ መረጃዎችን በመጠቀም በአጠቃቀም ደንቡ ወይም በንብረት ስምምነት መሰረት ለህግ ጉዳዮች የሚሆኑ ማሳወቂያዎችን ለመላክ እንደ አማራጭ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ እንዲረዱ እና እንዲቀበሉ። እንደዚህ ዓይነት መረጃዎች ላይ ማንኛውንም ለውጦች ሲያደርጉ ለኩባንያው ወዲያውኑ ማሳወቅ የእርስዎ ግዴታ ነው።