ግላዊነት ፖሊሲ
መግቢያ
ኢግል ሂልስ ፕሮፐርቲስ ኤሌ ኤል ሲ የትኛውንም ሁሉንም የ ኢግል ሂልስ ፕሮፐርቲስ ኤሌ ኤል ሲ ቅርንጫፎችን ጨምሮ “እኛ” የእርስዎን እርሶ የግል የሆኑ ንብረትዎን በማክበር እና ለዚህ ፖሊሲ ባለን የማስተዳደር ሀላፊነት አማካኝነት ድህንነትዎን ለመጠበቅ ሁሌም ቁርጠኛ ነን።
ይህ ፖሊሲ ከእርስዎ www.eaglehills.com ድህረ ገጻችንን ሲጎበኙ የምንሰበስበውን ወይም ሊያቀርቡ የሚችሉትን የመረጃ አይነቶች እና መረጃን የመሰብሰብ፣ የመጠቀም፣ የመጠበቅ፣ የመከላከል እና የማሳወቅ አሰራሮችን ዘርግተናል ይገልጻል ።
ይህ ፖሊሲ የምንሰበስበውን መረጃ ይመለከታል፡-
- በዚህ ድረገጽ ላይ
- በእርስዎ እና በዚህ ድህረ ገጽ መካከል የሚደረግ በኢሜል፣ በጽሁፍ እና በሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መልእክቶች።
- በሞባይል እና በዴስክቶፕ መተግበሪያዎች አማካኝነት ከዚህ ድረገጽ ሊያወርዷቸው የሚችሉ ለርስዎ የተበጁ በርስዎ እና በዚህ ድረ ገጽ መካከል ከበይነ መረብ ማሰሻው ውጭ የሚደረግ ግንኙነት
- በሶስተኛ ወገን ድረ-ገጾች እና አገልግሎቶች ላይ ከኛ ማስታወቂያ እና መተግበሪያዎች ጋር ግንኙነት ሲፈጥሩ ፤ ይህም እነዚያ መተግበሪያዎች ወይም ማስታወቂያ የዚህ ፖሊሲ አስፈንጣሪን ካካተቱ።
በሚከተሉ አካላት የተሰበሰበውን መረጃ አይመለከትም።
- ዝግ በሆነ መስመር ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ፣ በማንኛውም ሶስተኛ ወገን የሚሰራ ሌላ ማንኛውንም ድህረ ገጽ ጨምሮ፣ ወይም
- ከድህረ ገጹ ጋር ሊገናኝ የሚችል በማንኛውም መተግበሪያ ወይም ይዘት (ማስታወቂያን )አካቶ ማንኛውም ሶስተኛ ወገን።
መረጃዎን እና እንዴት እንደምናስተናግደው ፖሊሲያችንን እና አተገባበሮቻችንን ለመረዳት እባክዎ ይህንን ፖሊሲ በጥንቃቄ ያንብቡ። በእኛ ፖሊሲዎች እና አተገባበሮች ካልተስማሙ አማራጭዎ የእኛን ድረ-ገጽ አለመጠቀም ነው። ይህን በመጠቀም፣ በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ተስማምተዋል ፤ ይህ ፖሊሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለወጥ ይችላል። ለውጦችን ካደረግን በኋላ ይህን ድህረ ገጽ መጠቀም መቀጠሎ ለውጦቹን እንደ መቀበል ይቆጠራል ፤ ስለዚህ እባክዎ ማሻሻያዎች ካሉ ለማረጋገጥ በየጊዜው ፖሊሲውን ይመልከቱት።
ስለእርስዎ ስለምንሰበስበው መረጃ እና እንዴት እንደሚሰበሰብ
መረጃን ጨምሮ ከድረ-ገፃችን ተጠቃሚዎች ብዙ አይነት መረጃዎችን እንሰበስባለን፡-
- በግል ሊታወቁባቸው የሚችሉባቸው መረጃዎች ለምሳሌ እንደ ስም ፣ የፖስታ አድራሻ ፣ የኢሜል አድራሻ ፣ የፓስፖርት ቁጥር ፣ የንብረት መታወቂያ ወይም የስልክ ቁጥር (“የግል መረጃ”)
- ስለእርስዎ የሚያመለክት ፤ ነገር ግን በግለሰብ ደረጃ እርስዎን የማይለይ እና/ወይም
- ስለ በይነመረብ ግንኙነትዎ፣ የእኛን ድረ-ገጽ ለማግኘት ስለሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች እና የአጠቃቀም ዝርዝሮች።
ይህንን መረጃ የምንሰበስበው፡-
- በቀጥታ ከእርስዎ ለእኛ ሲሰጡን
- በአውቶማቲክ መንገድ በድረገጹ ላይ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ፤ በአውቶማቲክ የሚሰበሰበው መረጃ ፡- የአጠቃቀም ዝርዝሮችን፣ የአይፒ አድራሻዎችን እና በኩኪዎች፣ ዌብ ቢኮኖች እና በሌሎች የመከታተያ ቴክኖሎጂዎች የተሰበሰበ መረጃን ሊያካትት ይችላል።
- ከሶስተኛ ወገኖች ለምሳሌ ከንግድ አጋሮቻችን።
ለእኛ የሚሰጡን መረጃ
በድረ-ገፃችን ወይም በድር ጣቢያችን የምንሰበስበው መረጃ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡
- በድረ-ገጻችን ላይ ቅጾችን በመሙላት የሚሰጡት መረጃ። በእኛ ስፖንሰር አድራጊነት ወደ ተዘጋጀው የውድድር ወይም በማስታወቂያ ሲገቡ እና በድረ-ገፃችን ላይ ችግሮችን ሲጠቁሙ።
- በንግግር ልውውጦ መዛግብት እና ቅጂዎች (በኢሜል አድራሻዎች እኛን ካገኙን)።
- ለምርምር ዓላማዎች እንዲሞሉ ልንጠይቅዎ የምንችላቸው የዳሰሳ ጥናቶች ምላሾ
- በድር ገጹ ላይ ያሰፈሯቸው የፍለጋ ጥያቄዎችዎ።
የአጠቃቀም ዝርዝሮች፣ አይ ፒ አድራሻዎች፣ ኩኪዎች እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች
በድረ-ገጻችን ላይ እንቅስቃሴ እና ልውውጥ ሲያደርጉ ፣ ስለ መሳሪያዎ፣ የአሰሳ ድርጊቶችዎ እና ልምድዎ አንዳንድ መረጃዎችን በአውቶማቲካዊ ሁኔታ ልንሰበስብ እንችላለን፣ የሚከትሉትን ጨምሮ፡-
- የትራፊክ ውሂብን፣ የአካባቢ ውሂብን፣ ድርጊቶችዎን እና ሌሎች የመገናኛ መረጃዎችን እና በድረ-ገጹ ላይ የሚገኟቸውን እና የሚጠቀሙቧቸውን ግብዓቶች ጨምሮ ወደ ድረ-ገጻችን ያደረጉትን ጉብኝት ዝርዝሮች።
- የእርስዎን የአይፒ አድራሻ፣ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና የበየነ መረብ አሳሽ አይነት ጨምሮ ስለ ኮምፒውተርዎ እና የበይነመረብ ግንኙነትዎ መረጃ።
በአውቶማቲካዊ መንገድ የምንሰበስበው መረጃ አሃዛዊ መረጃ ነው። የእኛን ድረ-ገጽ ለማሻሻል እና የተሻለ እና የበለጠ ግላዊ የሆነ አገልግሎትን ለማቅረብ በሚከተሉት መልኩ ይረዳናል
- የተጠቃሚዎችን ቁጥር እና የአጠቃቀም ዘይቤን መተምበይ።
- ስለ ምርጫዎችዎ መረጃን በማከማቸት፣ እንደየግል ፍላጎቶችዎ ድረ-ገጻችንን እንድናስተካክል ያስችለናል።
- ፍለጋዎችዎን ያፋጥናል።
- ወደ ድረ-ገጻችን ከወጡ በኋላ ሲመለሱ እርስዎን መለየት ይችላል።
ለዚህ አውቶማቲክ መረጃ መሰብሰብ የምንጠቀምባቸው ቴክኖሎጂዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-
- ኩኪዎች (ወይም የአሳሽ ኩኪዎች)፡- ኩኪ በኮምፒውተርዎ ሃርድ ድራይቭ ላይ የተቀመጠ መጠነ ትንሽ ፋይል ነው። በአሳሽዎ ላይ ተገቢውን መቼት በማብራት የአሳሽ ኩኪዎችን አለመቀበል ይችላሉ። ነገር ግን፣ ይህን ምርጫ ከመረጡ የተወሰኑ የድረ-ገፃችንን ክፍሎች የማግኘት እድሉን ያጣሉ። ኩኪዎችን መቀበል እንዲከለክል የበየነ መረብ አሳሽ መቼቶን ካላስተካከሉ በቀር ፣ አሳሾን ወደ ድረገጻችን ሲያመላክቱት ሲስተማችን ኩኪዎችን ይሰጣል።
- ፍላሽ ኩኪዎች፡- አንዳንድ የድረ-ገጻችን ገፅታዎች ስለምርጫዎችዎ እና ወደ ፣ ከ እና ድረ-ገጻችን ላይ ስለምርጫዎ እና የአጠቃቀም መንገድ መረጃ ለመሰብሰብ እና ለማከማቸት በኮምፒተርዎ ውስጥ የተከማቹ ነገሮችን (ወይም የፍላሽ ኩኪዎችን) ሊጠቀሙ ይችላሉ። ፍላሽ ኩኪዎች ለበየነ መረብ አሳሽ ኩኪዎች ጥቅም ላይ በሚውሉበት ተመሳሳይ የአሳሽ መቼቶች አይተዳደሩም።
- ዌብ ቢከኖች፡- የድረ-ገጻችን ገፆች እና ኢሜይሎቻችን ዌብ ቢኮኖች በመባል የሚታወቁ (ወይንም ግልጽ gifs ፣ የፒክሰል መለያዎች እና ነጠላ-ፒክስል gifs ተብለው የሚታወቁ) ትናንሽ ኤሌክትሮኒክስ ፋይሎችን ሊይዙ ይችላሉ ፤ እነርሱም ኩባንያው ለምሳሌ እነዚያን ገጾች የጎበኙ ወይም ኢሜል የከፈቱ ተጠቃሚዎችን እና ለሌሎች ተዛማጅ የድረ-ገጽ ስታቲስቲክስ ለመቁጠር ይፈቅዱለታል። (ለምሳሌ ፡- የአንዳንድ ድረ-ገጽ ይዘት ታዋቂነት መመዝገብ እና የስርዓት እና የሰርቨር ዘወትራዊ ብቃትን ማረጋገጥ ነው።)
የእርስዎን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም
ማንኛውንም የግል መረጃን ጨምሮ ስለእርስዎ የምንሰበስበውን ወይም ለእኛ የሰጡንን መረጃ እንጠቀማለን
- የእኛን ድረ-ገጽ እና ይዘቱን ለእርስዎ ለማቅረብ።
- ከእኛ የሚጠይቁትን መረጃ ወይም አገልግሎት ለእርስዎ ለመስጠት።
- ላያቀረቡት ማንኛውንም ሌላ አላማ ለማሟላት።
- የማለቂያ ጊዜ፣ የክፍያ መጠየቂያ እና የእድሳት ማስታወቂያዎችን ጨምሮ ማሳወቂያዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ።
- ግዴታዎቻችንን ለመወጣት እና በእኛ እና በእርስዎ መካከል ከተደረጉ ኮንትራቶች የሚመጡትን መብቶችን ለማስከበር ፣ የሂሳብ አከፋፈል እና የመሰብሰብን ጨምሮ።
- በድረ-ገጻችን ላይ ስለሚደረጉ ለውጦች ወይም ስለምናቀርበው ማንኛውም ፕሮጀክት ወይም አገልግሎት ለእርስዎ ለማሳወቅ።
- በድረ-ገፃችን ላይ ኢንተራክቲቭ ስሪትፕች ላይ እንዲሳተፉ ለማስቻል።
- በሌላ በማንኛውም መንገድ መረጃውን ሲያቀርቡ ልንገልጽ እንችላለን።
- ከእርስዎ ፈቃድ ጋር ለማንኛውም ሌላ ዓላማ።
እንዲሁም ስለራሳችን እና የሶስተኛ ወገኖች ፕሮጀክቶች እና አገልግሎቶች እርስዎን ሊስቡ ስለሚችሉ ጉዳዮችን እርስዎን ለማግኘት የእርስዎን መረጃ ልንጠቀም እንችላለን። መረጃዎን በዚህ መንገድ እንድንጠቀምበት ካልፈለጉ፣ እባክዎን በ info@eaglehills.com ኢሜል አድራሻ ያግኙን።
የእርስዎን መረጃ ይፋ ማድረግ
ስለተጠቃሚዎቻችን የተዋሃደ መረጃን እና ማንንም የማይለይ መረጃን ያለ ገደብ ልንገልጽ እንችላለን።
በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ እንደተገለጸው የምንሰበስበውን ወይም እርስዎ ያቀረቡትን የግል መረጃ ልንገልጽ የምንችለው፡-
- ለቅርንጫፎቻችን እና አጋሮቻችን።
- ለንግድ ስራችን ድጋፍ የምንጠቀምባቸው ተቋራጮች፣ አገልግሎት ሰጪዎች እና ሌሎች ሶስተኛ ወገኖች
- ለገዢ ወይም ለሚመጣ ሌላ ተተኪ ባለቤት ከውህደት፣ መልሶ ማዋቀር፣ መልሶ ማደራጀት፣ መፍረስ ወይም ሌላ ሽያጭ ወይም ሁሉንም የኩባንያው ሙሉ ወይም ውስን ንብረቶች ማስተላለፍ ፣ በሂደት ላይ ያለ ወይም እንደ ኪሳራ፣ ማጣራት ወይም ተመሳሳይ ሂደት፣ በኩባንያው የተያዘው የግል መረጃ ለምሳሌ እንደ ድረ-ገፃችን ተጠቃሚዎች ከሚተላለፉ ንብረቶች መካከል አንዱ ነው።
- ያቀረቡትን ዓላማ ለመፈጸም
- መረጃውን ከፈቃድዎ ጋር ሲያቀርቡ በእኛ ለተገለጹ ሌሎች ማንኛውም ዓላማ።
እንዲሁም የእርስዎን የግል መረጃ በሚከተሉት ምክንያት ልንገልጽ እንችላለን፡-
- ለማንኛውም የመንግስት ወይም የተቆጣጣሪ ጥያቄ ምላሽ መስጠትን ጨምሮ ማንኛውንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣ ህግ ወይም ህጋዊ ሂደት ለማክበር።
- የአጠቃቀም ውላችንን ወይም የሽያጭ ውላችንን እና ሌሎች ስምምነቶችን ለማስፈጸም ወይም ለመተግበር፣ ለክፍያ እና የመሰብሰቢያ ዓላማዎችን ጨምሮ።
- የኩባንያውን፣ የደንበኞቻችንን ወይም የሌሎችን መብቶች፣ ንብረት ወይም ደህንነት ለመጠበቅ ይፋ ማድረግ አስፈላጊ ወይም ተገቢ ነው ብለን ካመንን። ይህ ለማጭበርበር መከላከያ እና የብድር ስጋት ቅነሳ ዓላማ ከሌሎች ኩባንያዎች እና ድርጅቶች ጋር መረጃ መለዋወጥን ይጨምራል።
የርስዎን መረጃ እንዴት እንደምንጠቀም ወይም እንደምንገልጽ ያሉን አማራጮች
ለእኛ የሚሰጡትን የግል መረጃ በተመለከተ ምርጫዎችን ልንሰጥዎ እንጥራለን። በመረጃዎ ላይ የሚከተሉትን ቁጥጥር ለእርስዎ ለማቅረብ ስልቶችን ፈጥረናል፡-
- የመከታተያ ቴክኖሎጂዎች እና ማስታወቂያ፡- ሁሉንም ወይም አንዳንድ የበየነ መረብ አሳሽ ኩኪዎችን ውድቅ እንዲያደርግ፣ ወይም ኩኪዎች በሚላኩበት ጊዜ እርስዎን ለማስጠንቀቅ አሳሽዎን ማስተካከል ይችላሉ። ኩኪዎችን ካሰናከሉ ወይም ካልተቀበሉ አንዳንድ የዚህ ጣቢያ ክፍሎችን የማግኘት እክል ሊያጋጥሞ ወይም በትክክል እንደማይሰሩ እባክዎ ልብ ይበሉ።
- ለሶስተኛ ወገን ማስታወቂያ የእርስዎን መረጃ ይፋ ማድረግ፡- ለማስታወቂያ ዓላማ ግላዊ መረጃዎን አጋር ወይም ወኪል ላልሆኑ ሶስተኛ ወገኖች እንድናካፍል የማይፈልጉ ከሆነ፣ ጥያቄዎን ወደ info@eaglehills.com በመላክ መውጣት ይችላሉ።
- ከኩባንያው የማስተዋወቂያ ቅናሾች፡- የራሳችንን ወይም የሶስተኛ ወገኖችን ፕሮጄክቶችን ወይም አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ የኢሜል አድራሻዎን ወይም የመገኛ አድራሻዎን ኩባንያው እንዲጠቀም ካልፈለጉ በ info@eaglehills.com ጥያቄዎን የሚገልጽ ኢሜል በመላክ መርጠው መውጣት ይችላሉ።
የእርስዎን መረጃ ማግኘት እና ማረም
ወደ ድህረ ገጽ ኢ-ሰርቪስ በመግባት የግል መረጃዎን መገምገም እና መለወጥ ይችላሉ። በ info@eaglehills.com ላይ በማነጋገር ስለእርስዎ የያዝነውን ማንኛውንም የግል መረጃ እንዲሻሻልዎ መጠየቅ ይችላሉ።
የውሂብ ደህንነት
የእርስዎን ግላዊ መረጃ ከአጋጣሚ ጥፋት እና ከፍቃድ ወጭ ጥቅም ላይ ከመዋል ፣ አጠቃቀም፣ ለውጥ እና ይፋ ከመደረግ ለመጠበቅ የተነደፉ እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርገናል። የሚያቀርቡልን ሁሉም መረጃዎች ከፋየርዎል ጀርባ ደህንነታቸው በተጠበቁ ሰርቨሮች ላይ ተቀምጠዋል።
በሚያሳዝን ሁኔታ በበይነመረብ በኩል የመረጃ ስርጭት ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም። የግል መረጃዎን ለመጠበቅ የተቻለንን ብንሰራም ወደ ድረ-ገጻችን የሚተላለፉትን የግል መረጃዎችዎን ደህንነት ማረጋገጥ አንችልም። ማንኛውም የግል መረጃ ማስተላለፍ በራስዎ ሃላፊነት ስር ነው። በድረ-ገጹ ላይ ለተካተቱት ማንኛቸውም የግላዊነት መቼቶች ወይም የደህንነት እርምጃዎችን ለተወጡባቸው መንገዶች ተጠያቂ አይደለንም።
በግላዊነት ፖሊሲያችን ላይ የተደረጉ ለውጦች
በግላዊነት ፖሊሲያችን ላይ የምናደርጋቸውን ማናቸውንም ለውጦች በዚህ ገጽ ላይ መለጠፍ የእኛ መመሪያ ነው። የግላዊነት ፖሊሲው ለመጨረሻ ጊዜ የተከለሰበት ቀን በገጹ አናት ላይ ተለይቷል። ማናቸውንም ለውጦች ለመፈተሽ የእኛን ድረ-ገጽ እና ይህንን የግላዊነት ፖሊሲ በየጊዜው የመጎብኘት ሃላፊነት የእርስዎ ነው።
የመገኛ አድራሻ
ስለዚህ የግላዊነት ፖሊሲ እና የግላዊነት አተገባበሮቻችን ማንኛውም አይነት ጥያቄ ወይም አስተያየት ካለዎት በ info@eaglehills.com ያግኙን።