ርዕስ፦ (Eagle Hills) & Broad ዘላቂ የግንባታ ቴክኖሎጂን ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለማስተዋወቅ በጋራ ይሰራሉ

Eaglehills
Eaglehills

(Eagle Hills) and Broad 100% በ ፋብሪካ የተመረተ፣ ዝቅተኛ ካርቦን መጠን ያለው እና ምንም ኮንክሪት የማይጠቀም የ “Holon (ሆሎን)” የሕንፃ ቴክኖሎጂን ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (UAE) ለማስተዋወቅ የሚያደርጉትን አጠቃላይ ትብብርን አሳውቀዋል። ይህ ሽርክና በአየር ንብረት ለውጥ የኑሮ ጥራት እና ግልፅነት ደረጃን ለማሳደግ ከአረብ ኤምሬትስ 2031 ራዕይ ጋር በሚስማማ መልኩ የሀገሪቱን ዘላቂ እና ኃላፊነት ያለው የመኖሪያ ልማት ለመርዳት ያለመ ነው። ሁለቱ ኩባንያዎች በጥልቀት በመተባበር የሙከራ ፕሮጀክት በጋራ ይጀምራሉ።

በብሮድ የተገነባው “ሆሎን” የግንባታ ቴክኖሎጂ በዝቅተኛ ካርቦን፣ ኮንክሪት የሌላቸው፣ ኃይል ቆጣቢ ሕንፃዎችን ለመፍጠር በፋብሪካ የተሠሩ ክፍሎችን የሚጠቀም የግንባታ አብዮታዊ አቀራረብ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ ቻይናን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት በተሳካ ሁኔታ የተተገበረ ሲሆን
አሁን ደግሞ በአረብ ኤምሬቶች ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲታይ ተዘጋጅቷል። በ (Eagle Hills) እና በ Broad መካከል ያለው አጋርነት ይህንን የፈጠራ ቴክኖሎጂ ወደ ክልሉ ማምጣት ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት ለሚደረገው ጥረትም አስተዋጽኦ ያደርጋል።

በ UAE ውስጥ የሚጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት ይህንን ዘላቂ የግንባታ ቴክኖሎጂ ለመቀበል ለሌሎች ሀገሮች አርአያ ሆኖ ያገለግላል ። ይህ የግንባታ ኢንዱስትሪ የካርቦን አሻራ መቀነስ ብቻ ሳይሆን በክልሉ ውስጥ ኃላፊነት ያለው እና ሥነ ምህዳራዊ ተስማሚ ልማትንም ያበረታታል። ፕሮጀክቱ ለ 2031 ከአረብ ኤምሬትስ ራዕይ ጋርም ይጣጣማል ።

በ (Eagle Hills) እና በ Broad መካከል ያለው አጋርነት በ UAE እና በክልሉ ውስጥ ዘላቂ ልማት ለማስፋፋት ጉልህ እርምጃ ነው። የ “ሆሎን” የግንባታ ቴክኖሎጂ ማስተዋወቅ አካባቢን ብቻ ሳይሆን ለነዋሪዎች የኑሮ ጥራትንም ያሻሽላል። በዚህ አጋርነት UAE ዘላቂ ግንባታ ውስጥ መሪ ትሆናለች።

ስለ ሽርክናው አስተያየት ሲሰጥ የ Eagle Hills መስራች እና ሊቀመንበር መሐመድ አላባር እንዲህ ብለዋል፦ “ከ COP28 ጋር በማጣመር ይህ ትብብር በ UAE ሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ ለዘላቂነት እና ለኢኮ-ግንዛቤ ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል። ፕሮጀክቱ ለዘላቂነት ልምምዶች እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግላል። ይህ ልማት በአቡ ዳቢ ውስጥ ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተገነባ በአይነቱ የመጀመሪያው ነው። ከ15 እስከ 30 ፎቅ የሚሸፍን 100% በፋብሪካ የተሠራ የመኖሪያ ግንብ ሲሆን በ6 ወር ውስጥ የሚጀመር እና ከ6 ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው። ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ፕሮጀክት በግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደ ምሳሌያዊ ለውጥ ሆኖ ያገለግላል፤ ይህም የካርቦን ልቀትን፣ የኃይል ውጤታማነትን እና የውሃ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልን ያረጋግጣል። ይህ የግንባታ ቴክኖሎጂ የሚከተሉትን ጨምሮ አዳዲስ ባህሪያትን እና ዘዴዎችን ያቀርባል፦

  • 100% በፋብሪካ የተሰራ (ምንም የተለመደ ቁሳቁስ፣ አሸዋ ወይም ኮንክሪት የለም)
  • ከ 90% እስከ 100% የኃይል ቆጣቢ
  • 100% የቤት ውስጥ አየር ጥራት
  • 100% ከአቧራ እና ቆሻሻ መከላከያ
  • 100% መልሰው ጥቅም ላይ የዋሉ የግንባታ ቁሳቁሶች
  • 100% የድምፅ ስርገትን የሚከላከል
  • በግንባታ ሥራዎች ወቅት 0% ብክለት
  • የግንባታ ወጪው ከተለመደው የግንባታ ወጪ ጋር ተመሳሳይ ነው”

“በዘላቂ ህንፃዎች ቁጥር በአለም አቀፍ ደረጃ 14 ኛ ደረጃ ላይ በመሆኗ፣ UAE ለዚህ መስክ ትልቅ አስተዋፆ አድርጋለች። ከ 900 በላይ ታዳሽ ሀይልን የሚጠቀሙ ሕንጻዎችን በመገንባት በምርጥ30 ሕንጻዎች ዝርዝር ውስጥ የምትገኝ ብቸኛዋ የክልሉ ሀገር ናት” ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም Eagle Hills ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር በመሆን የግንባታ ሥራዎችን መልክ ለመለወጥ እና በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ መዘጋጀቱን አፅንዖት ሰጥቶ ገልጿልል። ይህ የበለጠ ወጪዎችን እና ልቀቶችን ይቀንሳል፣ ለአካባቢ ተስማሚ እና ዘላቂ የመኖሪያ እና የንግድ ፕሮጀክቶች ላይ ለመሥራት እድል ይሰጣል።

ስለ Eagle Hills፦

Eagle Hills በአቡ ዳቢ ላይ መሰረቱን ያደረገ የግል ሪል እስቴት ኢንቬስትሜንት እና ልማት ኩባንያ ሆኖ በከፍተኛ እድገት ባላቸው ዓለም አቀፍ ገበያዎች ውስጥ አዳዲስ የከተማ ማዕከላት ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የሚገኝ ነው። መጠነ ሰፊ የሪል እስቴት ፕሮጄክቶችን በማዘጋጀት ላይ በማተኮር፣ Eagle Hills ቅይጥ አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎችን ነድፎ ይገነባል። እነዚህ ማህበረሰቦች በአከባቢው ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ እሴት የሚጨምሩ ስማርት ፕሮጄክቶችን ለመገንባት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም ላይ ይምረኮዛሉ። ኩባንያው በአሁኑ ጊዜ በ UAE፣ ኦማን፣ ባህሬን፣ ግብፅ፣ ዮርዳኖስ፣ ሞሮኮ፣ ኢትዮጵያ፣ ሰርቢያ፣ አልባኒያ እና ክሮኤሺያ ውስጥ ፕሮጀክቶችን እያካሄደ ነው።

www.eaglehills.com

ስለ Broad & Broad Holon፦

BROAD Group በ 1988 በቻይና የተመሰረተ የግል ድርጅት ሲሆን “ለሰው ልጅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ” ሲባል፣ ምድርን በፈጠራ፣ ሃይል ቆጣቢ እና ዘላቂ የባለቤትነት ቴክኖሎጂዎች የመጠበቅ ተልእኮ አለው። ዋና መሥሪያ ቤቱን ቻንግሻ ሁናን የሆነው BROAD፤ BROAD Air Conditioning, Clean Air Technology, Nearly Zero Energy Building, Energy Service, Renewable Resources, & BROAD Sustainable Building ጨምሮ የሚከተሉትን ንዑስ ኩባንያዎች ባለቤት ሲሆን ምርቶቹን ከ 80 በላይ አገራት ወደ ውጭ ይልካል።
BROAD “ሆሎን” በዓለም ላይ 100% በፋብሪካ በተሠሩ ከፍተኛ ሕንጻዎች ላይ ስልታዊ ምርምር እና ልማት የተሰማራ ብቸኛው ኩባንያ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ፈጠራ፣ ዘላቂ እና ዘላቂ ቴክኖሎጂ ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አብዮታዊ አቀራረብ ሲሆን ዝቅተኛ የካርቦን፣ ኮንክሪት የሌለበት እና የኃይል ቆጣቢ መፍትሄዎችን ይሰጣል።

en.broad.com

ስለ Eagle Hills

Eagle Hills በአቡ ዳቢ ላይ የተመሠረተ የግል ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት እና ልማት ኩባንያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ዕድገት ገበያዎች ውስጥ በተቀላቀለ አጠቃቀም የመዳረሻዎች ልማት ላይ ያተኮረ ነው። እነዚህ ማህበረሰቦች ለአከባቢው ኢኮኖሚ ከፍተኛ እሴት የሚጨምሩ ብልህ እና ዘላቂ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የቅርብ ጊዜ ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማሉ። ኩባንያው በሞሮኮ፣ በአልባኒያ፣ በባህሬን፣ ክሮኤሺያ፣ ኢትዮጵያ፣ ዮርዳኖስ፣ ላቲቭያ፣ ኦማን፣ ሰርቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ይገኛል።

ስለ Eagle Hills ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት www.eaglehills.com ን ይጎብኙ።

Error: Contact form not found.